ስለ ማህበሩ ምንነት

የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር የትራንስፖርት ባለስልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 468/97 ስለማኀበራት መቋቋም በአንቀፅ 13 እና 14 በሰፈረው መሰረት በጥቅምት 02/ 2003 ዓ.ም. አስራ አምስት (15) አባላትንና ሃያ ሦስት (23) ተሸከርካሪዎችን ይዞ በደረጃ 2-ለ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ ከወደብ (ጂቡቲ) እስከ ወደብ (ሞጆ) የደረቅ ጭነት አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ በዋናነት የተቋቋመው በሌሎች ተመሳሳይ ማህበሮች ይቀርቡ የነበሩትን ምሬቶች ሙሉ ሙሉ መልስ ለመስጠት ነው፡፡ ማህበሩ የማህበሩ አባላቶች በሚመርጧቸው በበላይነት በስራ አመራር ቦርድ የሚመራ ሲሆን በስሩም አንድ ጠቅላላ ስራ አስኪያጅ፣ አንድ የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴና ሦስት የስራ ክፍሎች አሉት፡፡ በተጨማሪም የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያሳልጡለት ሁለት ማለትም በሞጆና በጂቡቲ የከፈታቸው ማስተባበሪያ ቅርጫፎች አሉት፡፡