እንኳን ደህና መጣችሁ

የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር ሁሌም የእናንተን ደንበኞቻችንን ፍላጎት በበቂ ሁኔታ ለማስተናገድ እንሰራለን፡፡ አገልግሎታችንን ቀልጣፋና አስተማማኝ ለማድረግ የማህበሩ አመራርና መላው ሰራተኞቻችን በትጋት በመስራት የናንተን የደንበኞቻችንን እርካታ መጨመር ተቀዳሚ ተግባራችን ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ

ውጤታማ የመረጃና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት

yegna-transport-data-managements
የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ውጤታማ ለማድረግ አጠቃላይ የማኀበሩን አባላት ብዛት፣ የተሸከርካሪዎች ብዛት፣ አይነት እና የመጫን አቅም፣ እንዲሁም በየዕለቱ ማኀበሩ የሚያከናውናቸውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መዝግቦ ይይዛል፡፡ የማኀበሩን የሰው ኀይልና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ይይዛል፡፡ ማኀበሩ የሚያደርገውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በተመለከተ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚከሰቱ የመንገድ ትራፊክ የተሳፋሪ የእግረኛ የ3ኛ ወገን ጉዳዮች መዝግቦ ይይዛል የተሸከርካሪ ግጭቶችንና አደጋዎችን ይመዘግባል፡...
ተጨማሪ ያንብቡ

ፍትሃዊና ግልፅ የአባላት ተሸከርካሪዎች የስምሪት አገልግሎት

yegna-transport-trucks
የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር የአባል ተሸከርካሪዎች የስምሪት ፕሮግራም በዕኩልነት ላይ በመመስረት በማዘጋጀትና በወጣው የስምሪት ፕሮግራም መሠረት መፈፀሙን በመከታተል ፍትሃዊ ስምሪት ያረጋግጣል፡፡ ግልፅ የተሸከርካሪዎች ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት በአባላት መካከል የስምሪት አድልኦ እንዳይፈጠር ያረጋግጣል፡፡ ከማኀበሩ አባላት ውጭ የሆኑ ተሸከርካሪዎች ሥምሪት እንዳይሰጣቸው ይቀቆጣጠራል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ

አስተማማኝና ቀልጣፋ የጭነት አገልግሎት

yegna-transport
የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር ለደንበኞቹ አስተማማኝና ውጤታማ የጭነት አገልግሎት ለመስጠት ተሸከርካሪዎችን በወቅቱ አስፈላጊውን ኢንሹራንስ እንዲኖራቸውና በወቅቱ እንዲታደስ ያደርጋል፡፡ የተሽከርካሪዎቹን የቴክኒክ ደህንነት በየወቅቱ በመከታተል አስፈላጊውን ሰርቪስና ጥገና እንዲደረግላቸው ያደርጋል፡፡ ተሸከርካሪዎች በወቅቱ ተጠግነው ወደ ስራ ካልገቡ በፍጥነት በሌላ ተሸከርካሪ ጭነቱ እንዲጓጓዝ ያደርጋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት

yegna-transport-gps-technology
የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር ዘመኑ ያፈራቸውን የጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ቴክኖሎጂዎችን (ጂፒኤስ) በመጠቀም ለማህበሩ አባላት ስለ ንብረታቸው (መኪና) ደህንነትና የስራ እንቅስቃሴ በወቅቱ ያደርሳል፡፡ የአሰራር ስርዓቱን በዘመናዊ የዳታቤዝ አስተዳደር በማገዝ ለደንበኞቹ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም ለባለድርሻ አካሎቹ ተደራሽ ለመሆን በድረ ገጻችንና በማህበረሰብ ሚዲያ (በፌስቡክ፣ በቲውተር፣ ጉግል ፕላስና ዩቲውብ) በንቃት ይሳተፋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ

ልዩነታችን

የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበርን ልዩ የሚያደረገው የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር ገና ከጅምሩ የተቋቋመው በሌላ ማህበር ውስጥ በነበሩ አባላቶች ነው፡፡ ነገር ግን በነበሩበት ማህበር የነበረው አሰራር ግልፅነት የጎደለውና በተደጋጋሚ በተደረገው የማስተካከያ ጥረት ተፈላጊው ውጤት ስላለተገኘ ከማህበሩ በመውጣት የኛን ማህበር ለማቋቋም ተገደናል፡፡ በመሆኑም የየኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር አባል ለመሆን ሲወስኑ በሌሎች ተመሳሳይ ማህበራት የነበሩ መልካም ተሞክሮዎች በመውሰድና እጥረቶቻቸውን በማስተካከል በከፍተኛ የስራ ተነ...
ተጨማሪ ያንብቡ