ከአባልነት ስለማቋረጥ፣
የማኀበር አባልነት በሚከተሉት ሁኔታ ሊቋረጥ ይችላል፡-
- አባሉ ከማህበሩ በፈቃዱ ለመልቀቅ ጥያቄ ሲያቀርብና ማኀበሩ የሚፈለግበትን ሰነድ የወሰደውን ንብረት በሠነድ ሲያስረክብ፣
- በማኀበሩ አባልነት ያስመዘገበው ተሸከርካሪ ከሚሰጠው አገልግሎት ማኀበሩን ሳያሳውቅ ከአቅም በላይ ባልሆነ ምክንያት ከ30 ቀናት በላይ ከስምሪት ያልተሳተፈ ወይም በብልሽት ምክንያት ለተከታታይ ሶስት ወራት ከሥምሪት ውጭ ከነበረ እና ለማኀበሩ ካላመለከተ ፣
- የማኀበሩን አባላት የጋራ ጥቅምና ጤናማ የሥራ ሁኔታ በማወክ ፣ለማኀበሩ ደንብና የአሰራር መመሪያዎች መከበር ሕገ-ወጥ እና እንቅፋት የሆነ ሥራ ላይ በመሣተፍ ጥፋት ከፈጸመ የሥራ አመራር፣
- ቦርዱ አባሉን ከጥፋቱ ለማረም ጥረት በማድረግ ሊታረም አለመቻሉን ሲያረጋግጥ በውስጠ ደንብ መሠረት ከማህበሩ አባልነት ሊታገድ ይችላል፡፡