የአባል መብትነና ግዴታ፣
በጭነት ትራንስፖርት ማኀበሩ አባል የሆነ የተሸከርካሪ ባለንብረት የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡-
- ማኀበሩ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች በመገኘት የመምረጥም ሆነ የመመረጥ እኩል መብት ይኖረዋል.
- ማህበሩ በሚሰጠው ማንኛውም አገልግሎት እኩል የመጠቀም መብት ይኖረዋል፣
- በማኀበሩ ያለውን የአባልነት መብት ከራሱ ውጪ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ የግል መብት ሲሆን ፣መብቱንም የሚጠበቅለት ይሆናል፣
- አንድ የማኀበር አባል በአንድ ተሸከርካሪ ከአንድ ማኀበር በተጨማሪ ወደ ሌላ ማኀበር ሁለት ቦታ ሊመዘገብ አይችልም ከነበረበት ማኀበር መሸኛ በመውሰድ ወደሚፈልገው ማኀበር መቀየር ይችላል፡፡
- ማኀበሩ የሚተዳደርበትን ደንብ ፣የሚሰራባቸውን መመሪያዎች እና ከትራንስፖርት አካላት በየጊዜው ለጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት መሻሻል ማደግ የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች ጠይቆ የማግኘትና የመውሰድ መብት አለው፣
- በማናቸውም የማህበሩ መደበኛና አስቸኳይ የጠቅላላ አባላት ስብሰባ ላይ የመሳተፍ ፣ስለማኀበሩ የስራ እንቅስቃሴ ማደግና መጠናከር፣ሊኖር ስለሚገባው ቀጣይ የአሰራር ማሻሻያ እና የሚስተዋሉ የአተገባበር ችግሮችን ለመፍታት የሚረዱ አስተያየቶችንና የውሣኔ ድምፅ የመስጠት፣
- የራሱ ተሸከርካሪ የሰራበትን ሂሳብ ከወጪ ቀሪ በወቅቱ የማግኘት መብት አለው፣
- በአባልነት ከተመዘገበበት ማኀበር በራሱ ፈቃድ ለመልቀቅ ቢፈልግ ዕዳ ወይም ዕገዳ ከሌለበት መሸኛ የማግኘት መብት አለው፣
የማኀበር አባል የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩታል፡-
- የማኀበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ የሥልጣን ውክልና በተሰጠው የስራ አመራር ቦርድ የሚሰጠውን የጋራ ስራ ለመፈፀም እንዲያስችል የሚተላለፉ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን መፈጸም
- ስለ ትራንስፖርት በመንግስት ሚወጡ ደንብና መመሪያዎች አክብሮ በስራ ላይ ማዋል፣
- አገልግሎት በሚሰጥበት ተሸከርካሪ ላይ የቴክኒክ ችግር ሲገጥመው ለማኀበሩ ጽ/ቤት ወይም በአቅራቢያው ላለው የሥምሪት ጽህፈት ቤት ማሳወቅና በማኀበሩ ጋራዥ የማስጠገን፣
- በመደበኛና ከመደበኛ ውጭ በማኀበሩ የሚሰጠውን የሥምሪት ትዕዛዝ መፈጸም፣
- ስለሚያከናውነው የጭነት ትራንስፖርትና በጉዞ ወቅት ስላጋጠመው አጠቃላይ ሁኔታዎች አስፈላጊውን መረጃ ለዚሁ ስራ ለተቋቋሙ መረጃ ማዕከላት መስጠት፣
- ለሚጭነው ማንኛውም ጭነት ማኀበሩ ባሠራው መሠረት ውል የመቀበልና በውሉ መሠረት የመፈፀም፣
- በተሸከርካሪው የሚጓጓዙ ዕቃዎችን በአግባቡ ተረክቦ በተሟላ ጥንቃቄ ወደ አስፈላጊው ቦታ የማድረስ፣ ኃላፊነት ተግባራዊ እንዲሆን ለማኀበሩ ሙሉ ኃላፊነት መስጠት
- ስለተሸከርካሪዎች የጉዞ አፈፃጸም የወጡ መስፈርቶችን መጠበቅና የመረጃ ቅፆችን በአግባቡ በመጠቀም ሥራ ላይ እንዲውል ማኀበሩ በኃላፊነት እንዲመራለት ማድረግ፣
- ተሸከርካሪው ላይ የማኀበር አርማ፣ እስቲከር መለጠፍ፣ዓርማው የማኀበሩን አድራሻ እንዳይዝ ከማኀበሩ ጋር መስራት፣
- የማኀበሩ አባል በተሸከርካሪው ላይ የሚሰሩ አሸከርካሪና ረዳት በሚቀጥርበት ጊዜ ውል መፈፀም አለበት ፡፡ የውሉ ኮፒም ለተደራጀበት ማኀበር ያቀርባል ከማኀደሩ ጋርም እንዲያያዝ ይደረጋል፡፡
- አባሉ በተሸከርካሪው ላይ የሚሠሩ ሾፌሮችና ረዳቶች በውል የማይቀጥር ከሆነ ማኀበሩ ኃላፊነት በመውሰድ ይቀጥርለታል፡፡