የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር ድርጂታዊ መዋቅር፣
ማኀበሩ ለመደራጀት በፈለገበት የደረጃ መስፈርት የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ማንኛውም የጭነት ትራንስፖርት ማኀበር የሚከተለው ድርጅታዊ መዋቅር ይኖረዋል፡፡
- ጠቅላላ ጉባዔ፣
- የውስጥ ኦዲትና ኢንስፔክሽን፣
- የሥራ አመራር ቦርድ፣
- ሥራ አስኪያጅ፣
በሥራ አስኪያጅ ሥር፡-
- አስተዳደር፣
- የንብረትና ፋይናንስ፣
- የመረጃ፣ ትራፊክ ደህንነት (Safety Unit) እና የኤች. አይ. ቪ. ኤድስ መከታተያ፣
- የዕቅድ እና የገበያ ጥናት፣
- የኦፕሬሽንና ሥምሪት፣
- የስራ ክትትልና ቁጥጥር፣
- የቅርንጫፍ ቢሮዎች አስተዳደር፣
- የቅርንጫፍ ቢሮዎች ሂሳብ ክፍል እና ገንዘብ ሰብሳቢ፣
- የቅርንጫፍ ቢሮዎች የሥምሪት መረጃ ሙያተኛ፣
ከላይ የተዘረዘሩትን የሥራ አካላት የያዘ ድርጅታዊ አወቃቀርን ይከተላል፡፡ ድርጅታዊ አወቃቀር በተቻለ ሁኔታ የሥራ ሂደትን መሰረት ያደረገ /Process Oriented/ የሆነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በደረጃ መስፈርቱና በሞዴሉ ላይ በተዘረዘረው የሰው ሀይል ልክ አመቺ የስራ ቢሮ ይኖረዋል የቢሮ መገልገያ መሣሪያዎችና ህትመቶች ተዘጋጅተው ስራ ላይ መዋል አለባቸው፡፡