ውጤታማ የመረጃና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አገልግሎት

የኛ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 2-ለ የደ/ጭ/ማመ/ባ/ማህበር የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ውጤታማ ለማድረግ አጠቃላይ የማኀበሩን አባላት ብዛት፣ የተሸከርካሪዎች ብዛት፣ አይነት እና የመጫን አቅም፣ እንዲሁም በየዕለቱ ማኀበሩ የሚያከናውናቸውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መዝግቦ ይይዛል፡፡ የማኀበሩን የሰው ኀይልና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ይይዛል፡፡ ማኀበሩ የሚያደርገውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በተመለከተ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚከሰቱ የመንገድ ትራፊክ የተሳፋሪ የእግረኛ የ3ኛ ወገን ጉዳዮች መዝግቦ ይይዛል የተሸከርካሪ ግጭቶችንና አደጋዎችን ይመዘግባል፡፡ ስለ ትራፊክ ደህንነት ለአባላቱ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ በአባላቱ ተሸከርካሪዎች የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን አስፈላጊ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል፣ ተገቢ የሆኑ የደህንነት መረጃዎችን በተዘጋጀ ፎርማት ለአራጁ አካል አደጋውንና የጉዳት መጠኑን የሚገልጽ መረጃ ያስተላልፋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *