የየኛ የትራንስፖርት ኦፕሬሽን ክፍል

ማኀበራችን የስምሪት እንቅስቃሴውን የሚመራ የኦፕሬሽን ክፍል ሲኖረው፣ የስራ ኃላፊው በሥራ አስኪያጁ አቅራቢነት በስራ አመራር ቦርዱ ፀድቆ የተመረጠ ነው፡፡ ዘርፉ ተጠሪነቱ ለሥራ አስኪያጁ ነው፡፡ ይህ የስራ ክፍልም በዋናነት የሚያከናውናቸው ስራዎች በወጣው የስምሪት ፕሮግራም መሠረት መፈፀሙን እያረጋገጠ የተሻለ አገልግሎት ለተጠቃሚው ለማቅረብ የሚያስችል የስምሪት ጥናት አድርጎ በማቅረብ፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ የማኀበሩን አባል ተሸከርካሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል፡፡ የፊሊት ማናጅመንት ቴክኖሎጂን አገልግሎት ላይ በማዋልና በአባላት ተሸከርካሪዎች ላይ የቴክኒክ ደህንነትና ብቃትን ቁጥጥር በማድረግ፣ ተስተካክለውም ለሥምሪት መቅረባቸውን ያረጋግጣል፡፡ በአባላት መካከል በሥምሪት አድልኦ ያለመደረጉን የሚያረጋግጥ ስርዓት ይፈጥራል፡፡ ከማኀበሩ አባላት ውጭ የሆነ ተሸከርካሪዎች ሥምሪት እንዳይሰጣቸው በመቆጣጠር በአጠቃላይ የስራ ክንውኑን በወቅቱ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *