የየኛ አስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል

የማኀበራችን የንብረትና ገንዘብ አስተዳደር ኃላፊ ቀጥታ ተጠሪነቱ ለማኀበር ሥራ አስኪያጅ ሲሆን ዋና ተግባሮቹም የማኀበሩን የንብረትና ገንዘብ በአግባቡ መያዙንና በሕግና ሥርዓት ሥራ ላይ መዋሉን በማረጋገጥ የማኀበሩ አጠቃላይ ንብረቶች መዝግቦ በመያዝ፣ በትክክልም ለማኀበሩ አገልግሎት መዋላቸውን ይቆጣጠራል፡፡ የማኀበሩን የገቢና ወጪ ሂሳቦች አሠራር ትክክለኛነትና በመመሪያው መሠረት ሥራ ላይ መዋላቸውን በመቆጣጠር ስለማኀበሩ ንብረቶች አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ስለገቢና ወጪ የማኀበር ሂሳቦች አያያዝና አጠቃቀም የተሟላ መረጃ ያዘጋጃል፡፡ በሥሩ ያሉትን የሂሳብ ሹምና ገንዘብ ቤት ሠራተኞችን በአግባቡ በመምራት፣ በመቆጣጠርና በመደገፍ የማኀበሩን ንብረትና የገንዘብ አሠራር በተሟላና በብቁ ባለሙያዎች አደራጅቶ መምራት የሚያስችለውን ዕቅድ ያወጣል፣ ሲፀድቅለትም ተግባራዊ በማድረግ በሥራ ክፍሉ ያለውን አጠቃላይ የስራ ክንውን ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ለሚመለከተው አካልም ያቀርባል፡፡ ማኀበሩ ትክክለኛውን የሥራ ዝርዝር የሚያሳይ መዝገብ እንዲኖረው ያደርጋል፣ ይህም መዝገብ ከዋናው ጽ/ቤት ሳይወጣ በጥንቃቄ ተጠብቆ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡ የሰራተኞችን ጉዳይ በተመለከተም የስራ ቅጥር ያደርጋል፣ እድገት፣ ዝውውርና የአመት ዕረፍት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ የዲሲፒሊን ሁኔታ ያያል፣ ያጣራል፣ስንብት ይፈፅማል፣ ማኀበሩ የሚያገኛቸው ገቢዎች በሙሉ ለማኀበሩ ዓላማ ማስፈጸሚያነት መዋሉን ይቆጣጠራል፣ ስለ ማኀበሩ የንብረት አያያዝና የገንዘብ አጠቃቀም የተሟላ ሪፖርት በአመቱ መጨረሻና እንደተጠየቀ ለማህበር አመራር አካላትና ለስራ አስኪያጁ ያቀርባል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *