የየኛ መረጃና ትራፊክ ደህንነት ክፍል

የመረጃና ትራፊክ ደህንነት ክፍል

የማኀበራችን የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ክፍል አጠቃላይ እንቅስቃሴዎችን መረጃ ይሰበስባል፣ ያደራጃል ያቀነባብራል፡፡ የሥራ ኃላፊው በስራ አስኪያጁ አቅራቢነት በስራ አመራር ቦርዱ ፀድቆ የተመረጠ ሲሆን ተጠሪነቱም ለስራ አስኪያጁ ነው፡፡ የዚህ ክፍል ዋና ዋና ተግባሩም አጠቃላይ የማኀበሩን አባላት ብዛት ፣ የተሸከርካሪዎች ብዛት ፣ አይነት እና የመጫን ችሎታ፣ እንዲሁም በየእለቱ ማኀበሩ የሚያከናውናቸውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መዝግቦ መያዝ፡፡ የማኀበሩን የሰው ኀይልና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዝና መጠበቅ፡፡ በአደራጁ አካል በትራንስፖርት ባለስልጣን በተዘጋጁ ፎርሞች መሠረት መረጃዎችን በጽ/ቤቱ በኩል በየወሩ ለአደራጅ አካል ማስተላለፍ፡፡

ማኀበሩ የሚያደርገውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በተመለከተ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚከሰቱ የመንገድ ትራፊክ፣ የተሳፋሪ፣ የእግረኛ የ3ኛ ወገን ጉዳዮች መዝግቦ ይይዛል፡፡ የተሸከርካሪ ግጭቶችንና አደጋዎችን በመመዝገብ ስለ ትራፊክ ደህንነት ለአባላቱ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ በአባላቱ ተሸከርካሪዎች የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን አስፈላጊ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል፣ ተገቢ የሆኑ የደህንነት መረጃዎችን በተዘጋጀ ፎርማት ለአራጁ አካል አደጋውንና የጉዳት መጠኑን የሚገልጽ መረጃ ያስተላልፋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *